የሳይክ ኢን አክሽን ክለብ የእንኳን ደህና መጣችሁ ዝግጅት ክንውን
በእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር ላይ ለታደማችሁ ሁሉ ምስጋናችንን ስንገልጽ በደስታ ነው! ዶክተር እንዳልካቸው ተሰራ እና የት/ት ቤቱ ሲኒየር መምህር ፕሮፌሰር ሃብታሙ ወንድሙ በፕሮግራማችን ላይ በመገኘት ለሰጡን ጠቃሚ ምክርና ማበረታታት ልዩ ምስጋና ልናቀርብላቸው እንወዳለን። የኢትዮጵያ ሳይኮሎጂ ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ሄኖክ ሀይሉ እና የኦልስታር ሳይኮሎጂ ማዕከል መስራች ለሆኑት ለአቶ ሂሳቡ ሓድጉ አክብረውን ስለመጡ፣ የመርሃ ግብራችን ተካፋይ ስለሆኑ...

