Loading Events
  • This event has passed.

« All Events

የሳይክ ኢን አክሽን ክለብ የእንኳን ደህና መጣችሁ ዝግጅት ክንውን

November 12, 2024

በእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር ላይ  ለታደማችሁ ሁሉ ምስጋናችንን ስንገልጽ በደስታ ነው!

ዶክተር እንዳልካቸው ተሰራ እና የት/ት ቤቱ ሲኒየር መምህር ፕሮፌሰር ሃብታሙ ወንድሙ በፕሮግራማችን ላይ በመገኘት ለሰጡን ጠቃሚ ምክርና ማበረታታት ልዩ ምስጋና ልናቀርብላቸው እንወዳለን።

የኢትዮጵያ ሳይኮሎጂ ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ሄኖክ ሀይሉ እና የኦልስታር ሳይኮሎጂ ማዕከል መስራች ለሆኑት ለአቶ ሂሳቡ ሓድጉ አክብረውን ስለመጡ፣ የመርሃ ግብራችን ተካፋይ ስለሆኑ በተጨማሪም ለሳይክ ኢንፎ መጽሄት ህትመት እንዲሁም በክለባችን ለሚደረጉ የተለያዩ ክንውኖች ሊያግዝ የሚችል የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ቃል በመግባት አብሮነታቸውን ስለገለፁልን ከልብ እናመሰግናለን፡፡

በተጨማሪም የሳይክ ኢን አክሽን ክለብ ተጠሪ የሆኑት መምህር አቶ ወርቅነህ ለዚህ ዝግጅት መሳካት ላደረጉልን እገዛ እናመሰግናለን ።

በመጨረሻም ፕሮግራማችን የአዲስ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ብቻ ሳይሆን የመዝናኛ አይነት መርሃ ግብር እንዲሆን ላደረገልን ሳይኮሎጂስት እና የሙዚቃ ባለሞያ አቶ አላዛር ተስፋዬ እንዲሁም ለኪነ ፈውስ ሙዚቀኞች ልዩ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን።

 

ሚዲያ  እና ኮምኒኬሽን ዲፓርትመንት
ሳይክ ኢን አክሽን ክለብ
ሳይኮሎጂ  ት/ት ቤት
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

Details

  • Date: November 12, 2024